☰
Home
Bible
Articles
asdenaki teamirat
Lessons
Audio Lessons
Video Lessons
Textual Lessons
Worship Songs
Audio Songs
Video Songs
Lyrics
Meet Jesus
Contact Us
Previous
Next
0:00
play radio in a popup player
or
Article Archive
April 2025
የሀይማኖት ደጋፊ አይደለሁም ፤ ከሀይማኖት ይልቅ ህያውነት በእኔ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው። ሀይማኖት ውስጥ ህያውነት አለ ብዬ አላምንም። ህያውነት ያለው የህይወት ምንጭ በሆነው በኢየሱስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ ፤ አውቃለሁ። ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ፣ አዳኝነት እና በመስቀል ላይ ስለተሰራው የመቤዠት ስራ በምንም ነገር ሳይሸፋፈን እና ሳይደበቅ ሲነገር ስሰማ እጅግ ደስ ይለኛል።
አኬ
ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers
ከተወሰኑ ጊዜዎች ወደዚህ በማህበራዊ ሚዲያ ከማያቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆች መካከል አሰባበኩ ለየት ያለብኝ የምወደው ልጅ ነው። ምንም እንኳን ሁሉን የሚለውን ጉዳይ ባልስማማበትም ወጣቶች ከገድላት ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በኢየሱስ ላይ እንዲያተኩሩ የሚከፍለው ዋጋ የሚደነቅ ነው። የእኔ ትልቁ ደስታ ሰው ከኦርቶዶክስ ወደ ጴንጤ ወይም ከጴንጤ ወደ ኦርቶዶክስ መምጣቱ ሳይሆን ህያው ከሆነው ኢየሱስ ጋር ሲገናኝ ፤ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ሲመጣ ነው።
ሰሞኑን ይህ ልጅ በገዛ ወገኖቹ በተለይም መምህራን፣ ቀሳውስት፣ ወዘተ በሚባሉ ወገኖች "መናፍቅ ነው" በሚል እየተፈረጀና መገፋት እየደረሰበት እንዳለ ተገንዝቤአለሁ። በእኔ እምነት ይህ ባይሆን እና ልጁ የጀመረው ነገር ላይ ቀርቦ ማወያየት ተገቢ ይመስለኛል። ትውልዱ በወንጌል ላይ ፣ በኢየሱስ ላይ እንዲያተኩር ስራውን ይቀጥል።
ከዚያ ውጪ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቸኛዋ የመዳን መንገድ፣ እግዚአብሔርንም የኢትዮጵያን አምላክ ተደርጎ መውሰድ ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ የከፈለውን የመቤዠት ስራ እጅጉን ማሳነስ ስለሆነ ወጣቱ ከዚህ ጠባብነት ወጥቶ ኢየሱስን ብቻ ቢሰብክ ደስተኛ ነኝ።
አኬ እግዚአብሔር ይርዳህ፤ አይዞህ። እንወድሃለን !!
ይህንን ልጅ የምታውቁትና የምትወዱት አስተያየታችሁን ከታች ማስቀመጥ ትችላላችሁ። ተባረኩ!!
asdenaki teamirat
God is good All the time.
Daniel Amdemichael Limeles
There are no articles to display here.